Fana: At a Speed of Life!

በአርሲ ዞን 20 የአሸባሪው ሸኔ አባላት እጃቸውን በሰላም ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርሲ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች 20 የአሸባሪው ሸኔ አባላት ለመንግሥትና አባገዳዎች በሰላም እጅ መስጠታቸውን የዞኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ኮሚቴ ሰብሳቢና የዞኑ ዋና አስተዳደሪ አስታወቁ።
 
በሙኔሳ ወረዳ በተካሄደው ሰላም ኮንፍረንስ ላይ አባገዳዎች በአሸባሪው ሸኔ ላይ የውግዘት ውሳኔ አሳልፈዋል።
 
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአርሲ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ሙሳ ፎሮ እንደገለጹት፤ በወረዳው ሀገር ለማፍረስ ከተሰለፉ ጠላቶች ጋር መሰለፍን ያልፈቀዱ 20 የሸኔ አባላት እጃቸውን በሰላም ሰጥተዋል።
 
በተሳሳተ አመለካከት የሽብር ቡድኑን ተቀላቅለው ሲንቀሳቀሱ ቆይተው የአባገዳዎችን የውግዘት ውሳኔና ጥሪ ተቀብለው እጅ ሊሰጡ እንደቻሉ ገልጸዋል።
 
የአርሲ አባገዳዎች ‘ልጆቻችን ከባንዳ ጋር አይወግኑም፣ ሀገር አያፈርሱም፣ መክረን ገፅፀን እንመልሳለን’ ብለው ቃል በገቡት መሰረት አባላቱ ከጥፋት መንገድ በመለለስ እጃቸውን በሰላም መስጠታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
በሀሰት ፕሮፓጋንዳ ተታለው ጫካ ገብተው የነበሩት እነዚህ የአሸባሪው ሸኔ ቡድን አባላት ሰላማዊ መንገድ መምረጣቸውን ገልጸዋል።
 
አባገዳዎችና ማህበረሰቡ ባደረጉት የተቀናጀ ዘመቻ ቀደም ሲልም በርካታ የአሸባሪው ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስታውቀዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.