በእንግሊዝ ኢትዮጵያውያን የምዕራባውያን ጣልቃገብነትን የሚቃወም ሰልፍ እያካሄዱ ነው
አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን አንዳንድ ምዕራባውያን መንግሥታት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃገብነት የሚቃወም ሰልፍ እያካሄዱ ይገኛሉ።
ሰልፈኞቹ የእንግሊዝ መንግሥት በኢትዮጵያውያን የተመረጠው መንግሥት ላይ ጫና ከማድረግ እንዲቆጠብ እና እንግሊዝም ሆነች አሜሪካ ከኢትዮጵያ ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ ጠይቀዋል።
“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምርጫችን ነው፤ ሕዝባችንን ለዘመናት ሲያሰቃይ የቆየውን አሸባሪውን ህወሓት ‘ፈፅሞ አይሆንም’ እንለዋለን፤ የአፋር እና የአማራ ሕዝብ በሽብር ቡድኑ መሞት ይብቃ” የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችንም አሰምተዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!