የ ‘#No_More’ ዘመቻ የውጭ ጣልቃ ገብነቱ እስካልተነሳ ድረስ ይቀጥላል – የንቅናቄው አስተባባሪዎች
አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ዓለም የተጀመረው የ‘በቃ‘ ወይም ‘#No_More’ ሀሽታግ ዘመቻ አሜሪካ እና ሌሎች ሸሪኮቿ እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እስካላነሱ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል የንቅናቄው አስተባባሪዎች እና የትናንትናውን ሰልፍ በተለያዩ ከተሞች ያዘጋጁት ኢትዮጵያውያን።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የንቅናቄው ዓለም አቀፍ አስተባባሪ ነብዩ አስፋው ÷ በቅርብ የተጀመረው ንቅናቄው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ፣ ኤርትራውያን፣ ከምስራቅ አፍሪካ እና ሌሎች የአፍሪካ አገራት እንዲሁም የካሪቢያን አገራት ዜጎችን ማሳተፍ መቻሉን አንስተዋል።
በትናንትናው እለትም በአምስት አህጉራት እና ከ27 በላይ ከተሞች የተካሄደው ሰልፍ ታሪካዊ እና አንድነት የታየበት ነበር ብለዋል።
በቀጣይነትም አሜሪካ እና ሸሪኮቿ ከአላስፈላጊ ጫና እና የኢትዮጵያን እጅ ለመጠምዘዝ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ካላቆሙ ከሌሎች ወዳጆች ጋር የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንቀጥልበታለን ብለዋል።
በዋሽንግተን ዲሲ የሰልፉ አስተባባሪ የነበሩት ጣሰው መልከህይወት ÷ በበኩላቸው በኋይት ሀውስ ፊት ለፊት በነበረው ሰልፍ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለውን የተሳሳተ አካሄድ እንድትቀይር መጠየቁን ገልጸዋል።
ለሌሎችም ፍትህን ብቻ የምንፈልግ ፤ ያለንንም እውነት የማስረዳት ስራ ተሰርቷልም ነው ያሉት።
ይህ እንቅስቃሴ ፍትህን ብቻ መሻት ነውና ‘’አንሰር ኮሊሽን አፍሪካን አሜሪካን’’ የተሰኘው የመብት ተከራካሪ እና የአሜሪካን አምባገነንነት በመቃወም የሚታወቀው ‘’ብላክ አሊያንስ ፎር ፒስ ‘’አላማውን ደግፈው ከእኛ ጋር ቆመዋል ነው ያሉት አቶ ነብዩ።
በሰልፎቹ የአገር ደጀን መከላከያን በሁሉም መስኮች መደገፍ እንደሚገባ ፤ የኢትዮጵያ መንግስት አሁን እያደረገ ያለውን የአገርን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ስራም ከጎኑ እንደሚቆሙም ሰልፈኞቹ አንስተዋል ነው ያሉት አስተባባሪዎቹ።
በቀጣይነትም አሁን የታየው አንድነት በ’አይዞሽ ኢትዮጵያ’ እና በሌሎችም የድጋፍ ማሰባሰቢያ መድረኮች ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በአፈወርቅ አለሙ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!