በአሸባሪው ህወሓት የታጣውን ምርት በመስኖ ልማት ለማካካስ እየሠራን ነው – አርሶ አደሮች
አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ከባለፉት ዓመታት በተለየ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በአሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኃይል የታጣውን ምርት ለማካካስና በጦርነት የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ ጠንክረው እየሠሩ መሆናቸውን የባሕር ዳር ዙሪያ መስኖ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው በአማራና አፋር ክልሎች ላይ ወረራ በመፈፀም ንጹሃንን እየገደለ፣ ቤት ንብረታቸውን እያወደመ እንዲፈናቀሉ እያደረገ ይገኛል።
በበርካታ አካባቢዎችም የተዘሩ ሰብሎችን አጭዶ ወስዷል፤ አውድሟል፡፡
ይህንን የወደመውን ሰብል ለማካካስም በአማራ ክልል የመስኖ አማራጭ ባላቸው አካባቢዎች በትኩረት እየተሠራ ይገኛል፡፡
አርሶ አደር ቄስ ደሳለኝ ዓለም በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ ናቸው፤ የመስኖ ተጠቃሚም ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና የምትወጣበት አንዱ መንገድ ልማት ነው የሚሉት ቄስ ደሳለኝ ÷ በዘመቻው ግማሹ ወደ ጦር ግንባር ሲያመራ ሌላው በልማት ተሳታፊ መሆን አለበት ብለዋል፡፡
ባለፈው ዓመት 200 ኩንታል ሽንኩርትና የተትረፈረፈ የቲማቲም ምርት አምርተው እንደነበር የገለጹት አርሶ አደሩ ÷ ዘንድሮ ካለፈው ዓመት በተለየ መንገድ እያለሙ እንደሚገኙ ነው የገለጹት፡፡
መስኖን ተጠቅመው በሚያመርቱት ምርትም በአሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኃይል የተጎዱ አካባቢዎችን ታሳቢ በማድረግ ሌሎች ሰብሎችን በማምረት ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡
ሌላኛው አርሶ አደር ብርሃን አሰፋ እንደተናገሩት ÷ ያለ ስንቅ ጠላትን ማሸነፍ አይቻልም፡፡
በሰፊው በማምረት በዘመቻው ስንቅ ለማቅረብና የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ እየሠሩ እንደሆነ ነው ያስረዱት፡፡
በበጀት ዓመቱ በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በአዲስና በነባር መስኖ 6 ሺህ 223 ሄክታር መሬት የሚለማ ሲሆን ÷ ከዚህም 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዷል፡፡
የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይታየው ታረቀኝ ÷ ከባለፈው ዓመት በተለየ ዘንድሮ 68 ሄክታር መሬት በመስኖ ይለማል ብለዋል፡፡
በወረዳው በመስኖ ትርፍ በማምረት አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኃይል በከፈተው ጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን ለመደገፍ እየተሠራ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
በወረዳው የሚገኙ ሁሉም ቀበሌ አመራሮችና የግብርና ሙያተኞች እየተከናወኑ ያሉ የመስኖ ሥራ እንቅስቃሴዎችን መመልከታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!