Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ለአማራ ክልል ተፈናቃዮች የ73 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች ሕፃናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከስዊድን የልማት ተራድኦ ድርጅት በዩኒሴፍ በኩል ያገኘውን 73 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ለአማራ ክልል ተፈናቃዮች ድጋፍ አድርጓል።
 
የድጋፍ ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች እና ተፈናቃዮች በተገኙበት ተካሂዷል።
 
ከዚህ ተጨማሪም 3 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚያወጣ የዓይነት ድጋፍም ለተፈናቃዮቹ ተደርጓል።
 
የሴቶች ሕፃናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በአሸባሪው ህወሓት ምክንያት ለከፋ ማኅበራዊ ቀውስ የተጋለጡ ተፈናቃይ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
 
በስዊድን የልማት ተራድኦ ድርጅት ደጋፊነት እና በዩኒሴፍ አስተባባሪነት የተደረገው ድጋፍ የተፈናቃዮችን ችግር የሚያቃልል ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
የቀጥታ የገንዘብ ድጋፉ የተፈናቃዮችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ድጋፍ ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።
 
የዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የአማራ ክልል አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጫኔ ድጋፉ በክልሉ ከ45 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች የቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ የሚውል ነው ብለዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.