Fana: At a Speed of Life!

የጠ/ሚ ዐቢይ ውሳኔ ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በነፃነት ለማቆየት ያላቸውን ቁርጠኛ አቋም የሚያሳይ ነው -አቶ ወርቁ አይተነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደጦር ግንባር ማምራታቸው ከህዝባቸው ቀድመው በመገኘት እናት ሀገራቸውንና የሚመሩትን ህዝብ በነፃነት ለማቆየት ያላቸውን ቁርጠኛ አቋም የሚያሳይ ታሪካዊ ውሳኔ ነው ሲሉ ባለሃብት አቶ ወርቁ አይተነው ተናገሩ ፡፡
 
ጦርነት ከሚካሄድባቸው በአንዱ ግንባር ዘመቻ ላይ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ወርቁ ፥ ሃብት ከነፃነት በታች በመሆኑ ባለሃብቶች ዘመቻውን በሁሉም መስክ መደገፍ ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት፡፡
 
ባላሃብቱ አክለውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጦር ግንባር ዘምተው ዜጋው ከቤቱ መዋል በፍፁም አይጠበቅበትም፤ የመሪውን ፈለግ በመከተል ወደጦር ሜዳ መትመም ይጠበቅበታል እንጅ” ብለዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነቱን አፅንቶ የጋራ ጠላቱ የሆነውን ወራሪውንና አሸባሪውን ህወሓት መደምሰስ ይጠበቅበታል ያሉት አቶ ወርቁ፥ ኢትዮጵያ ማሸነፏ አይቀሬ ነው፤አትጠራጠሩ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
 
በዘላለም ገበየሁ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.