በመዲናዋ በአንድ ግለሰብ ቤት በርካታ ማህተሞች እና ቲተሮችን ጨምሮ ከፍተኛ የውሃ ማስተላለፊያ ተገጣጣሚ የቱቦ ብረቶች ተያዙ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአንድ ግለሰብ ቤት ፖሊስ ባከናወነው ብርበራ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ማህተሞች እና ቲተሮች እንዲሁም በግለሰብ እጅ መቀመጥ የሌለበት በርካታ ከፍተኛ የውሃ ማስተላለፊያ ተገጣጣሚ የቱቦ ብረቶች ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።
ብርበራው የተከናወነው ትናንት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አያት ዞን 3 መንገድ አምስት አካባቢ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል።
ብርበራው የአካባቢው ማህበረሰብ ባደረበት ስጋት ለፖሊስ በአካል ቀርቦ በሰጠው ጥቆማ መሰረት የተደረገ መሆኑንም ፖሊስ አስታውቋል።
በአማራ፣ በትግራይ፣ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ስም የተዘጋጀ 15 ክብ ማህተም እና 12 ቲተሮች፥ እንዲሁም በግለሰብ እጅ የማይፈቀዱ ከፍተኛ የውሃ ማስተላለፊያ ተገጣጣሚ የቱቦ ብረቶች ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር ውሎ ተገቢው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከልና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ዋና ኢንስፔክተር አራጌ እሸቴ ገልጸዋል።
ህብረተሰቡ አገርን እና ህዝብን ሊጎዳ የሚችል ተግባር ሲመለከትና ሲጠራጠር በፍጥነት መረጃ ለፖሊስ መስጠት በመቻሉ የተሻለ የህግ ማስከበር ስራ መስራት ተችሏል ተብሏል።
ሁሉም ሰው ዛሬ ነገ ሳይሰላች ትክክለኛ መረጃ በመስጠት አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ የ አሸባሪውን ህወሓት ቡድን ልክ ማስገባት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀላፊነት እንደሆነ ዋና ኢንስፔክተር አራጌ እሸቴ አሳስበዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!