Fana: At a Speed of Life!

በአውስትራሊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አሰባሰቡ

አዲስ አበባ፣ህዳር 18፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በአውስትራሊያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተቋቋመው ‘ሴቭ ኢትዮጵያ’ አስተባባሪነት በተዘጋጀ የበይነ መረብ መድረክ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ 178 ሺህ የአውስትራሊያ ዶላር ተሰበሰበ፡፡
በበይነ መረብ መድረኩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ እንድሪስ፣ የ‘ሴቭ ኢትዮጵያ’ ሊቀ መንበር አቶ አያሌው ሁንዴሳ እንዲሁም በግንባር ከሚገኙ የዳያስፖራ አባላት መካከል ደግሞ ነዓምን ዘለቀ እና ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ ተሳትፈዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን አጠናክረው ለጋራ ሀገራዊ እጣ ፈንታቸው በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ ቀርቧል፡፡
የምዕራብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ አባላት የሚሳተፉበት የሃብት ማሰባሰቢያ መድረክ በመካሄድ ላይ መሆኑን ከዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.