Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ‘ኢትዮጵያ ትጣራለች’ በሚል መርሃ ግብር 160 ሚሊየን ብር ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት በአዲስ አበባ በተካሄደው ‘ኢትዮጵያ ትጣራለች’ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ 160 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል።
 
ባለሃብቱ አቶ ወርቁ አይተነው 50 ሚሊየን ብር፣ ጎመጁ ኦይል ኢትዮጽያ 20 ሚሊየን ብር፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 5 ሚሊዮን ብር፣ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 2 ነጥብ 25 ሚሊዮን ብር፣ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 3 ሚሊዮን ብር፣ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ 1 ሚሊዮን ብር፣ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር፣ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ 1 ሚሊዮን ብር ለመለገስ ቃል ገብተዋል።
 
በመርሃ ግብሩ በርካታ ግለሰቦች፣ ተቋማት እና ድርጅቶችም በርካታ ገንዘብ ለመለገስ ቃል ገብተዋል።
 
ከገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር የተገኘው ገቢ ለመከላከያ ሠራዊቱ፣ ለአማራ ልዩ ሃይል፣ ለሌሎች የጸጥታ አካላት እንዲሁም ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች እንደሚውል መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.