የመስቀል ደመራ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በድምቀት እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስቀል ደመራ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በልዩ ልዩ ኃይማኖታዊ ሥነሥርዓት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡
በሥነሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ በርካታ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች፣ የእምነቱ ተከታዮችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።