Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሩጫ ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ለሜቻ ግርማ በፓሪስ ዳይመንድ ሊግ የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሩጫ ውድድር  የዓለም ክብረወሰን በመስበር አሸንፏል፡፡ አትሌት ለሜቻ ርቀቱን በ7 ደቂቃ 52 ሰከንድ 11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ክብረ ወሰን በመስበር ያሸነፈው፡፡ በዚህም በኬንያዊው አትሌት በ7 ደቂቃ 53 ሰከንድ 63 ማይክሮ ሰከንድ ተይዞ የቆየውን የርቀቱን ክብረ ወሰን ማሻሻል ችሏል፡፡ በሌላ በኩል ትናንት ምሽት በተካሄደው የፓሪስ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር አትሌት ለተሰንበት ግደይ…
Read More...

የሀድያ ሆሳዕና እና የአዳማ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ከተማ 3ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ ጥሩ ፉክክር በታየበት በዚህ ጨዋታ አዳማ ከተማ 3 ለ 0 እየመራ ቢቆይም ሀድያ ሆሳዕና ነጥብ መጋራት ችሏል። በጨዋታው የአዳማ ከተማን ሁለት ግቦች ዳዋ ሆቴሳ ሲያስቆጥር ቀሪዋን አንድ ግብ አዲስ…

የስድስት ሀገራት አትሌቶችን የሚያሳትፈው የአስመራ ማራቶን የፊታችን እሑድ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ጨምሮ የስድስት ሀገራት አትሌቶችን የሚያሳትፈው የአስመራ ማራቶን በመጪው እሑድ እንደሚካሄድ የኤርትራ ባህልና ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኤርትራ ባህልና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዘመዴ ተክሌ ÷በውድድሩ መርሐ ግብር የወንዶች ሙሉ ማራቶን እና የ10 ኪሎ ሜትር የሴቶች ውድድርመዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡…

ሪያል ማድሪድ እና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ  በቤሊንግሃም ዝውውር ሲስማሙ ሊዮኔል ሜሲ ወደ አሜሪካ ሊያቀና ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሪያል ማድሪድ እንግሊዛዊውን የቦሩሲያ ዶርትመንድ አማካይ ጁዲ ቤሊንግሃምን ለማስፈረም መስማማቱ ተሰምቷል። ሎስብላንኮዎች አማካዩን ለማስፈረም 113 ሚሊየን ፓውንድ የሚከፍሉ ሲሆን፥ ተጫዋቹም ስድስት አመታት የኮንትራት ውል እንደሚፈርም ይጠበቃል። ቤሊንግሃም ስሙ ከሊቨርፑል እና ሪያል ማድሪድ ሲያያዝ መቆየቱ ይታወሳል።…

ካሪም ቤንዜማ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ ለመቀላቀል ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ አጥቂ ካሪም ቤንዜማ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ኢቲሃደን ለመቀላቀል ተስማማ፡፡ ቢቢሲ ማምሻውን ይዞት በወጣው መረጃ የባለንድኦር አሸናፊው ቤንዜማ ሪያል ማድሪድን በመልቀቅ ከአል ኢቲሃደ ጋር የ3 ዓመት ውል ፈጽሟል፡፡ የ35 ዓመቱ ቤንዜማ በሪያል ማድሪድ ቆይታው 5 የሻምፒዮንስ ሊግና 4…

የአፍሪካ ዞን 4 የጎልፍ ስፖርት ሻምፒዮና ውድድር የመክፈቻ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ዞን አራት የጎልፍ ስፖርት ሻምፒዮና ውድድር የመክፈቻ መርሐ ግብር ጦር ኃይሎች በሚገኘው ጎልፍ ክለብ እየተካሄደ ነው፡፡ በመክፈቻ መርሀ ግብሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም…

የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛው ዙር የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ መካሄድ ጀምሯል። የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን ባዘጋጀው ውድድር ከስድስት ክለቦች የተውጣጡ ከ90 በላይ ስፖርተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። ውድድሩ በአዋቂዎችና በታዳጊዎች በሁለቱም ፆታ የሚካሄድ ሲሆን÷በቀጣይ በቱኒዚያ ለሚካሄደው…