Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ባህርዳር ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 1 አሸነፈ፡፡ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው የ16ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የጣና ሞገዶቹ ከመመራት ተነስተው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተከታታይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሶስት ነጥብ አስመዝግበዋል፡፡ ለባህር ዳር ከተማ ሀብታሙ ታደሰ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ፉአድ ፈረጃ ቀሪዋን አንድ ጎል አስቆጥሯል፡፡ የኢትዮ ኤሌክትሪክን ብቸኛ ጎል አብነት ደምሴ በ51ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶቹ…
Read More...

ኔይማር ጁኒየር እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ወደ ጨዋታ እንደማይመለስ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው ኮከብ ኔይማር ጁኒየር እስከታድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ወደ ጨዋታ እንደማይመለስ ተገልጿል፡፡ የ31 ዓመቱ የፊት መስመር አጥቂ ክለቡ ፒኤስጂ ሊልን 4 ለ 3 ባሸነፈበት ጨዋታ ባጋጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት ምክንያት ነው እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሜዳ የራቀው፡፡ ኔይማር በፒኤስጂ ቆይታው በቀኝ እግሩ ላይ…

በቶኪዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2023 የቶኪዮ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በወንዶች ማራቶን አትሌት ዴሶ ገልሚሳ ርቀቱን 2 ሰዓት 5 ደቂቃ 22 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆኗል፡፡ በተጨማሪም አትሌት መሀመድ ኢሳ 2ኛ እና አትሌት ጸጋዬ ከበደ ደግሞ 3ኛ በመውጣት ውድድሩን…

በፕሪሚየርሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን በማሸነፍ በድጋሚ ሊጉን መምራት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 1 በማሸነፍ በድጋሚ ሊጉን መምራት ጀምሯል፡፡ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው የ15ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አቤል ያለው እና እስማኤል ኦሮ አጉሮ የቅዱስ ጊዮርጊስን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ቢኒያም ጌታቸው የድሬዳዋ ከተማን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡ ውጤቱን…

የፕሪሚየር ሊጉ 16ኛ እና 17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የቀን ማስተካከያ ተደረገባቸው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ16ኛ እና 17ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ማስተካከያ ተደርጎባቸዋል። የፕሪሚየርሊጉ ከ14ኛ እና 17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች አክሲዮን ማህበሩ ባወጣው ፕሮግራም መሰረት በድሬዳዋ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ በ15ኛው ሳምንት የሶስተኛ ቀን ጨዋታ ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ ዝናብ…

በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ አትሌቶቹ ከተሳተፉባቸው ውድድሮች መካከል የ2023 የጃፓን ኦሳካ ማራቶን ውድድር ትናንት ሲካሄድ በዚህ ውድድር በሴቶች አትሌት ሄለን በቀለ እና  አትሌት በየኑ ደገፋ አንደኛ እና ሁለተኛ በመውጣት ሲያሸንፉ በወንዶች…

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በበርሚንግሃም የ3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በእንግሊዝ በርሚንግሃም በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሩጫ ድል ቀንቷታል፡፡ አትሌቷ ርቀቱን በ8 ደቂቃ 16 ሰከንድ 69 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ያሸነፈቸው፡፡ በዚህም አትሌት ጉዳፍ አዲስ ክብረ ወሰን ለማስመዝገብ 9 ሰከንድ የቀራት መሆኑ…