ስፓርት
የሀላባን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የሩጫ ውድድር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሀላባን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የ8 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ተካሄደ።
“ሴራችን ለሰላማችን” በሚል ሀሳብ በተካሄደው የሩጫ ውድድር ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ውድድሩን ያስጀመረችው አትሌት ፋንቱ ምጌሶ “ሰላም ለሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ የሀላባ ብሄር የዘመን መለወጫ በዓሉን ከሰላም ጋር በማስተሳሰር መከበሩ ልዩ ያደርገዋል” ብላለች።
በውድድሩ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ የገንዘብና የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ሽልማት እንደተበረከተላቸው…
Read More...
በቶኪዮ ኦሊምፒክ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች ማስተላለፍ እንደማይቻል ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ጥር 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ የእጅ ምልክትን ጨምሮ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች ማስተላለፍ እንደማይቻል ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ።
ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በቀጣዩ ሃምሌ ወር በጃፓን ቶኪዮ በሚካሄደው ኦሊምፒክ ውድድር ላይ ለተወዳዳሪ አትሌቶች በተከለከሉ የደስታ አገላለጾች እና የሚያስተላልፏቸውን መልዕክቶች…
በፕሪምየር ሊጉ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መሪነቱን ተረከበ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተካሂደዋል።
ሁለተኛ ደረጃ ላይ የነበረው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወደ ድሬዳዋ በማቅናት 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡
በሌላ ጨዋታ መሪው ፋሲል ከነማ ወደ ሶዶ በማቅናት ከወላይታ ዲቻ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 1 በማጠናቀቁ ቢጫ…
የሴኔጋልና የሊቨርፑሉ አጥቂ ሳዲዮ ማኔ የአፍሪካ የዓመቱ ኮኮብ ተጫዋች ሆነ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን እና የሊቨርፑሉ አጥቂ ሳዲዮ ማኔ በአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) የአፍሪካ የዓመቱ ኮኮብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ፡፡
ሳዲዮ ማኔ የዓመቱ ኮኮብ ተጫዋችነት ሽልማትን ያገኘነው የቡድን አጋሩን ሞሃመድ ሳላህ እና የአልጀሪያና የማንቼስተር ሲቲውን የመስመር ተጫዋች ሪያድ ማህሬዝን አስከትሎ ነው።…
በቻይና በተካሄደ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱ ጾታዎች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
በቻይና በተደረገው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ሲያሸንፉ በሴቶች ምድብ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።
በውድድሩ በወንዶች አትሌት ብርሃን ንባባው ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ…
በፕሪምየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ መቐለ 70 እንደርታን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬ በተካሄደው 6 ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ መቐለ 70 እንደርታን አሸንፏል።
መቐለ 70 እንደርታን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የቅዱስ ጊርጊስን የማሸነፊያ ግቦች ሳላህዲን ሰዒድ እና አቤል ያለው ሲያስቆጥሩ፥ አሸናፊ ሀፍቱ…
6ኛው የብዙሃን ስፖርት በመስቀል አደባባይ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስድስተኛው ዙር የብዙሃን ስፖርት መርሃ-ግብር ዛሬ በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል።
አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግን ባህል ያደረገ ከተማ እና ህብረተሰብ መፍጠርን ዓላማ ባደረገው በዚህ ሁነት በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
የዛሬውም የብዙሃን ስፖርት መርሃ ግብር ለአዲስ አበባ አረንጓዴነት የድርሻዬን…