Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ለአፋር ክልል ተፈናቃዮች የ40 ሚሊየን ብር ድጋፍ አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል 40 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ድጋፉን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አስረክበዋል፡፡
ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ 30 ሚሊየኑ በጥሬ ገንዘብ የተበረከተ ሲሆን ÷10 ሚሊየኑ ደግሞ በአይነት የተደረገ ድጋፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የአፋር ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊት እና ከክልሉ ልዩ ሃይል ጋር በመቀናጀት አሸባሪውን እና ወራሪውን ህወሓት በመደመስሰ ያሳየው ድል የሚያኮረራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
የሲዳማ ክልል መንግስት እና ህዝብ ባለፈው አመት በአፋር ክልል በአንበጣ እና ጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ዜች ድጋፍ ማድረጉን ያስታወሱት አቶ አወል÷አሁን ላይ በሽብር ቡድኑ ለተፈናቀሉ ዜጎች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በበኩላቸው÷ የአፋር ህዝብ አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ ባደረገው ተጋድሎ ሊመሰገን ይገባል ማለታቸውን የአፋር መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
 
የሲዳማ ክልል ህዝብ እና መንግስትም በክልሉ በአሸባሪው ህወሓት ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
 
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.