Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራዎች የግል መገልገያ ዕቃዎቻቸውን ይዘው መግባት እንደሚችሉ የጉሙሩክ ኮሚሽን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገናን በዓል ለማክበር ወደ አገር ቤት የሚመጡ ዳያስፖራዎች የግል መገልገያ ዕቃዎቻቸውን ይዘው መግባት እንደሚችሉ የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
 
የጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
 
በመግለጫቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 1 ሚሊየን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ እንግዶችን ለማስተናገድ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
 
ጤናማ መንገደኞችን ማለትም ለህክምና የሚመላለሱ እና ዳያስፖራዎች የግል መገልገያ ዕቃዎቻቸውን ይዘው መግባት እንደሚችሉም ነው የገለጹት፡፡
 
የግል መገልገያ ዕቃዎች መመሪያ 51/2010 የንግድ ዕቃዎችን ይዞ መግባትን ይከለክላል ያሉት ኮሚሽነሩ÷ ይሁን እንጂ ነጋዴዎች አሁንም በተደጋጋሚ በመመላለስ ከመመሪያው ውጭ እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡
 
ይህም በህጋዊ ነጋዴዎች ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
ወደ ሀገር ቤት የሚመጡ ዳያስፖራዎች ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለተፈናቃዮች እና ለህክምና ተቋማት ቁሳቁስ ይዘው መምጣት እንደሚችሉም አስረድተዋል።
 
ኮሚሽኑ ዳያስፖራዎችን በአግባቡ ለማስተናገድ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጓልም ነው ያሉት፡፡
 
ኮሚሽኑ በህገወጥ ተመላላሽ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ሲወስድ መቆየቱን ያስታወሱት ኮሚሽነሩ÷አሁንም እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
 
በአልማዝ መኮንን
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.