ጅማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ለመከላከያ ሰራዊት ከ55 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አበረከቱ፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የ35 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያስረከበ ሲሆን÷ ድጋፉም ከዩኒቨርሲቲው የውስጥ ገቢ እና ከሰራተኞች ደመወዝ የተሰበሰበ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ የተመራ ልዑክ በአዲስ አበባ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በመገኘት ድጋፉን አስረክቧል።
ዶ/ር ጀማል እንደተናገሩት÷ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የአሁኑን ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ77 ሚሊየን ብር በላይ በገንዘብ፣ በዓይነት እና በሙያ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት በጥሬ ገንዘብ 16 ሚሊየን እና በአይነት 4 ሚሊየን ብር በድምሩ የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አስረክቧል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳ እንደገለጹት÷ ሰላማችንን ለማፅናት እየተዋደቀ ለሚገኘው ጀግናው መከላከያ ሰራዊት ይህኛው ለሁለተኛ ጊዜ የተደረገ ድጋፍ ነው፤ ወደፊትም ቀጣይነት ያላቸውን አበርክቶዎች ዩኒቨርሲቲው አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
በመከላከያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በተካሄደው ስነ ስርዓት ዩኒቨርሲቲው የ16 ሚሊየን ብር ቼክ ለመከላከያ ሰራዊት ሚንስተር ዲኤታ ማርታ ሉዊጂ አስረክቧል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ÷ ትምህርትም ሆነ ሌሎች ነገሮችን ማከናወን የሚቻለው የሀገር ደህነት ሲረጋገጥ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎቹ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና ይገባል ማለታቸውን ከዩኒቨርሲቲዎቹ ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!