Fana: At a Speed of Life!

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሒደት ሰልፍ ይዘው የቆዩ መራጮች እስኪመርጡ ይቀጥላል – ቦርዱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የድምፅ መስጠት ሒደቱ ከ12 ሰዓት በፊት ሰልፍ ይዘው የቆዩ መራጮች እስኪመርጡ ይቀጥላል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፡፡
በዛሬው ዕለት ከጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ በነቂስ በመውጣት ድምጹን እየሰጠ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሒደት ላይ መሆኑ ይታወቃል።
ቦርዱ ድምፅ የመስጠት ሒደቱ እስከ 12 ሰዓት ሠልፍ ላይ የነበረው ድምፅ ሰጪ ድምፅ ሰጥቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድምፅ የመስጠት ሒደቱ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49 (4) መሠረት ቦርዱ በልዩ ሁኔታ የድምፅ መስጫ ሰዓት ሊያራዝም እንደሚችል ይደነግጋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.