Fana: At a Speed of Life!

ለዳያስፖራው የተደረገው ጥሪ በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ጫና ይቀንሳል – የዳያስፖራ ኤጀንሲ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ለኢትዮጵያ ወዳጆች በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የተደረገው ጥሪ በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን የዲፕሎማሲና የሚዲያ ጫናን ከመቀነስ አንጻር አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሀመድ እድሪስ ገለጹ፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተመራ ባለው ብሔራዊ ኮሚቴ 6 ንዑሳን ኮሚቴዎች መካተታቸውን ጠቁመው÷ በንዑሳን ኮሚቴዎች ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ማኅበራት፣ የግል ተቋማት እና መገናኛ ብዙኃን መካተታቸውን አብራርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከዳያስፖራው ማሕበረሰብ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ እየሠራ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር መሀመድ÷ ለዚህም ከኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ጋር በመተባበር ዳያስፖራው ከሚኖርበት አገር ከመነሳቱ በፊት፣ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላና ወደ መጣበት ሲመለስየሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራትን ማዘጋጀቱን አንስተዋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ከዳያስፖራው ማሕበረሰብ በአገር ቤት የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮችን ለማዘጋጀት መነሳሳት መኖሩን የጠቆሙት ዶ/መሀመድ÷ ይህን ጥያቄ ለመመለስም ኤጀንሲው እየሠራ መሆኑን በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
ዳያስፖራው ለአገራዊ ጥሪው እየሰጠ ያለውን ምላሽ ታሳቢ በማድረግ÷ ከጉዞው ጋር ከዳያስፖራው ይቀርቡ የነበሩ የቪዛና ጉምሩክ አገልግሎቶች በባለድርሻ አካላት መቅረፍ መቻሉንም ነው የተናገሩት።
በሜሮን ሙሉጌታ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.