Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለቱርክ አፍሪካ አጋርነት ጉባኤ ኢስታንቡል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው ቱርክ ኢስታንቡል ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ቱርክ ያቀኑት በሦስተኛው የቱርክ አፍሪካ አጋርነት ጉባኤ  ላይ ለመሳተፍ  መሆኑ ታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢስታንቡል ሲደርሱም የሀገሪቱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና በቱርክ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሶስተኛው የቱርክ አፍሪካ አጋርነት ጉባኤ ዛሬ እና ነገ በኢስታንቡል ይካሄዳል።

39 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በዚህ ጉባኤ ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ እስካሁንም በርከት የሚሉት መሪዎች ኢስታንቡል መግባታቸው ነው የተነገረው።

ቱርክ ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መምጣቱ ይነገራል።

ሀገሪቱ በፈረንጆቹ 2002 ላይ በ12 የአፍሪካ ሀገራት ብቻ ኤምባሲ የነበራት ሲሆን፥ አሁን ላይ ግን በ43 የአፍሪካ ሀገራት ኤምባሲ ከፍታለች።

የዓየር መንገዷም ወደ 60 የተለያዩ የአፍሪካ መዳረሻዎች በመብረር ላይ ይግኛል።

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.