ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓን አስታወቀች፡፡
ድጋፉ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እና በሦስቱ ክልሎች ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ይውላል መባሉን በኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ድጋፉ በተመድ የዓለም የምግብ ፕሮግራም እና የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በኩል ሰብዓዊ እርዳታው ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች እንደሚደርስም ተገልጿል፡፡
ፈረንሳይ ከዚህ ቀደም ለ60 ሺህ አባወራዎች ዘር፣ የእርሻ መሳሪያ፣ መሰረታዊ የፍጆታ ቁሳቁሶችንና ለ130 ሺህ ተፈናቃዮች የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል የሚያስችል እንዲሁም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች የ500 ሺህ ዩሮ ድጋፍ ማድረጓ ይታወሳል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!