Fana: At a Speed of Life!

በጅማ በ338 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እየተከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ በ338 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነቡ ያሉ 26 ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እተከናወኑ ነው ተባለ፡፡
ሁሉም ፕሮጀክቶች ያሉበትን የግንባታ ሂደት የሚገመግም ጉብኝት ተካሂዷል፡፡
ፕሮጀክቶቹ የከተማዋን ነዋሪዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚፈቱ በመሆናቸው÷ ግንባታቸው በተያዘላቸው ጊዜ ሊጠናቀቁ እንደሚገባ የጅማ ከተማ ከንቲባ ነጂብ ራያ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
የከተማው ምክትል ከንቲባ ካሳሁን ጆብር በበኩላቸው፥ በከተማው እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች ከተያዘላቸው ጊዜ በፊት አስቀድመው እንዲጠናቀቁ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ነው የተናገሩት።
በጉብኝቱ ወቅት እንደተገለጸው÷ ከስምንት ወር በፊት ግንባታው የተጀመረው የኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት ግንባታው 96 በመቶ መድረሱንና በአሁኑ ወቅትም 300 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተናገድ ይገኛል ተብሏል፡፡
በሙክታር ጣሃ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.