የጉጂን ዞን ሠላም የሚያደፈርሱ የሸኔ አባላት በሠላም ኅብረተሰቡን እንዲቀላቀሉ አባገዳዎች ዳግም ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉጂን ዞን ሠላም የሚያደፈርሱ የአሸባሪው ሸኔ ቡድን አባላት በሠላም ኅብረተሰቡን እንዲቀላቀሉ የጉጂ አባ ገዳዎች ዳግም ጥሪ አቀረቡ፡፡
የጉጂ አባ ገዳዎች እንደገለጹት፥ የአሸባሪው ሸኔ አባላት በሠላም ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ጥሪ የቀረበው ለመጨረሻ ጊዜ እንደሆነ እና የጥሪውም ዓላማ ለዞኑ ሠላም ቅድሚያ በመስጠት ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
የጉጂ ዞን ባሕልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ አዶላ ሚኤሳ በበኩላቸው፥ የአባ ገዳዎቹ ጥሪ ለዞኑ ሠላም እና መረጋጋት ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመው፥ የዞኑ ማኅበረሰብ ለሠላማዊ ጥሪው ሁኔታዎችን በማመቻቸት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን የዘገበው ኦቢኤን ነው፡፡