Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት የደረሰበት የኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ዘረፋና ውድመት የደረሰበት የኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል የተወሰነ ቁሳቁስ ተሟልቶለት በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
 
የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ተፈራ ጎበዜ እንደገለጹት÷ የህወሓት ወራሪ ቡድን ከሆስፒታሉ የሚችለውን ዘርፎ፣ መውሰድ ያልቻለውንም ሙሉ በሙሉ በማውደም ለህዝብ ያለውን ጥላቻ በግልጽ አሳይቷል።
 
አካባቢው ከወራሪው ቡድን ነጻ በወጣ ማግስት ሆስፒታሉን ሥራ ለማስጀመር በተደረገው ቅንጅታዊ ጥረት የተወሰነ ቁሳቁስ ተሟልቶለት ካለፈው ሳምንት አንስቶ ለድንገተኛና ለወላድ እናቶች አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
 
እንዲሁም ከአለርት ሆስፒታል በተገኙ ማሽኖችና መድሃኒቶች ድጋፍም የቀዶ ሕክምና አገልግሎት መጀመሩንም ነው የተናገሩት።
 
በተያዘው ሳምንት የተመላላሽ ሕክምና አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የገለጹት ዳይሬክተሩ÷በቀጣይም ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የተጓደሉ የሕክምና ቁሳቁሶችን በማሟላት በሙሉ አቅሙ ሥራ ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
 
ለእዚህም ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደሥራ መገባቱን ዶክተር ተፈራ አመልክተዋል።
 
በቅርቡ አስተኝቶ ማከምና ሌሎች መደበኛ ሕክምናዎችን ለመስጠት ከ90 በመቶ በላይ የሆስፒታሉ ሠራተኞች ተሟልተው በእልህና በቁጭት ህብረተሰቡን ለማገልግል ወደ ስራ ማግባታቸውን አስረድተዋል።
 
የሆስፒታሉ የተኝቶ ሕክምና ክፍል ኬዝ አስተባባሪ ዶክተር ቁምላቸው መሰለ በበኩላቸው ፤ “የሽብር ቡድኑ ሆስፒታሉን ቢያወድመውም እውቀታችንና የሥራ ተነሳሽነታችንን መገደብ አልቻለም” ብልዋል።
 
በእልህና በቁጭት ያስጀመርነውን ሆስፒታል በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ እንዲገባ የሚጠበቅብንን ሁሉ እናደርጋለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
ህብረተሰቡን ጭምር በማስተባበር የሆስፒታሉን አካባቢ በማጽዳት ለእይታ ምቹ ከማድረግ ባለፈ የተለያዩ ግብዓቶችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
 
“በቅርቡም የሕክምና አገልግሎቱን በተሻለ ሁኔታ በመስጠት ህብረተሰባችንን እንደምንክስና ጠላትን እንደምናሳፍር አልጠራጠርም” ብለዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.