Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው የአቮካዶ ዘይት ፋብሪካ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው የአቮካዶ ዘይት ፋብሪካ ስራ መጀመሩ ተገለፀ፡፡

ዋይ ቢ ኤም የተሰኘው የአቮካዶ ዘይት ፋብሪካው በ104 ሚሊየን ብር በይርጋለም ግብርና ማቀነባበርያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተቋቋመና የአቮካዶ ዘይት በማምረት ወደ ውጭ የሚልክ ነው፡፡

ከ40 ሺህ ገበሬዎች ጋር ትስስር በመፍጠርም አቮካዶን ወደ ዘይት በመቀየር ወደ አውሮፓ እንደሚልክ የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ጎበና ገልፀዋል፡፡

ፋብሪካው ስራ ከጀመረ ሁለት ሳምንት ያስቆጠረ መሆኑንም ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እንደ አቶ ታመነ ገለፃ ÷የፋብሪካው ስራ መጀመር ለአካባቢው አርሶ አደሮች ቋሚ ገቢ መፍጠር የቻለ ሲሆን ÷ምንም አይነት ግብዓት ከውጭ ማስገባት ሳያስፈልግ የውጪ ምንዛሬን በማስገኘት ረገድ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

 

በይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ3ዓመት በፊት ስራ የጀመረው ሌላኛው ” ሳንቫዶ ” የተሰኘው የአቮካዶ ዘይት ፋብሪካ ከ88 ሺህ አርሶ አደሮች ጋር ትስስር በመፍጠርና ምርቱን በመሰብሰብ ለግብዓትነት ተጠቅሞ ያመረተውን የዘይት ምርት ወደ ኔዘርላንድ እየላከ ይገኛል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.