Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች በድህረ ጦርነት ላይ ያተኮረ ውይይት በቦንጋ ከተማ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
በጦርነቱ ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንድ ጠላትን አሸንፈው የተወረሩ አካባቢዎችን ነፃ ማውጣት ችለዋል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናግረዋል፡፡
ከጦርነቱ በኋላ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል ከወዲሁ ውይይት ማድረግና መፍትሄ ማስቀመጥ ተገቢ ነውም ብለዋል፡፡
ዛሬ በተጀመረው ወቅታዊ ውይይት ከክልሉና ከስድስት ዞኖች የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
በተስፋዬ ምሬሳ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.