በሆሳዕና በእሳት አደጋ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወደመ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሆሳዕና ከተማ ትናንት ሌሊት በተከሰተ የእሳት አደጋ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት መውደሙን ፖሊስ አስታወቀ።
በከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኘነት ማስተባበሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ካሳ ሊዕሊሶ እንደገለፁት፥ የእሳት አደጋው የደረሰው በከተማው ሊች አምባ መንደር 1 በተለምዶ ታይዋን ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትናንት ሌሊት አምስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ነው።
በአደጋው አስር የልብስ ስፌት አገልግሎት መስጫ ክፍሎች፣ አልባሳትና የልብስ መስፊያ ማሽኖች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን ጠቁመዋል።
የእሳት ቃጠሎው ወደ ሌሎች ቤቶች እንዳይዛመትና የከፋ ችግር እንዳያስከትል ህብረተሰቡና የፀጥታ አካላት ባደረጉት የተቀናጀ ርብርብ መቆጣጠር መቻሉን ተናግረዋል።
አደጋው በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት እንደሌለ ያመለከቱት ዋና ኢንስፔክተር ካሳ፥ የወደመው ንብረትም ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመትም አስታውቀዋል።
የእሳት አደጋው መንሰዔ ለጊዜው ባይታወቅም ፖሊስ ጉዳዩን አስመልክቶ ምርመራ እያደረገ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!