በአሸባሪዎቹ ቡድኖች ጉዳት ደርሶበት የነበረው የአጣዬ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ስራውን ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪዎቹ ህወሃት እና ሸኔ ቡድኖች ከፍተኛ ገዳት የደረሰበት የአጣዬ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውን መጀመሩ ተገለፀ፡፡
የትምህርት ቤቱ ሱፐርቫይዘር አቶ ማሙሽ ሲከፋኝ፥ ትምህርት ቤቱ አንጋፋና በክልሉ ካሉ ውጤታማ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን በጥፋት ሀይሎች በተደጋጋሚ የጉዳት ሰለባ በመሆኑ በትምህርት ቤቱ ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን አስታውሰዋል፡፡
የትምህርት አስተዳደሩ በደረሰው ጉዳት ተስፋ ሳይቆርጥ የአጥፊ ቡድኖቹ እቅድ እንዳይሳካ ትምህርት ለማስጀመር ከመምህራን ጋር ተግባብቶ የማስተማር እንቅስቃሴ መጀመራቸውንም ገልፀዋል፡፡
የትምህርት ቤቱ መምህራን በበኩላቸው፥ ካለው ጫና ተላቀው በቀረው ትንሽ የትምህርት ግብዓት የመማር ማስተማር ስራውን በተሻለ የስነልቦና ዝግጅት መጀመራቸውንም ተናግረዋል፡፡
የተለያዩ አካላት ችግሮቹን መጥቶ ከመመልከት በዘለለ የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ ለማድረግ እንዲረባረብ ተጠይቋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!