ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው÷ የገና በዓልን በላሊበላ ስናከብር ውድ የሆነውን እሴታችንን ለዓለም የምናስተዋውቅበት ነው ብለዋል። የገና በዓል የእምነት ብቻ ሳይሆን ባህልና ማንነትን ጨምሮ የሚከበር መሆኑንም ገልጸዋል።
አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን ንጹሐንን ጨፍጭፎና ብዙ ንብረት አውድሞና ዘርፎ ቢሄድም በዓሉን ስናከብር የተጎዱ ዜጎችን ልብ የሚጠግን ሀብትና ንብረትን የሚመልስ ተግባር በመፈጸም አጋጣሚውን መጠቀም እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።
በዓሉን በላሊበላ የሚያከብሩ በተለይ ዳያስፖራዎች ይህን መልዕክት በመተግበር ሀብትና ንብረት የወደመባቸው ዜጎች መልሶ በሚተካበት መንገድ ላይ የራሳቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
በተለየ መልኩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸውም ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ ያቀረቡት።
የአማራ ክልል ህዝብም ሆነ መላ ኢትዮጵያውያን በዓሉን ሲያከብሩ ከተረፋቸው ሳይሆን ካላቸው በመቀነስ የተጎዱ ወገኖች ተመልሰው እንዲቋቋሙ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉም ዶክተር ይልቃል ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!