በውስጥና በውጭ የተከፈቱብንን ጦርነቶች በድል የመወጣት አኩሪ ታሪካችን የሚደገምበት የታሪክ አውድ ውስጥ ነን – ዶክተር አብርሃም በላይ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊያን በየዘመናቱ በግልጽ በውጭና በውስጥ ሃይሎች የተከፈቱብንን ጦርነቶች አሳልፈን በመስዋዕት አገርን ያቆየን አኩሪ ታሪክ ያለን ህዝቦች ነን አሉ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ።
ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ምረቃ እና ልዩ የጀግንነት ተግባር ለፈፀሙ የሠራዊቱ አባላት በተዘጋጀ የሽልማትና ዕውቅና ስነስርዓት ላይ ነው።
ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ የተከፈቱባትን ጦርነቶች በድል የመወጣት አኩሪ ታሪካችን የምንደግምበት የታሪክ አውድ ውስጥ እንገኛለን ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ያጋጠማት በአይነቱ የተለየ እና የውጭ ሃይሎች ግድድር እና ጫና ለመቀልበስ የሚያስችል ደፋር ትልም የማስቀመጥ የአብርሆት ተግባር በህብረት መተለም የሚጠይቅ የአመራር ተግባር እንደነበር ጠቅሰዋል ሚኒስትሩ፡፡
ቀዳሚ ምዕራፎቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ብልህና ቆራጥ አመራር በድል ታጅቦ የተረጋገጠው ዘመቻ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ የጥምር የጸጥታ ሃይሎች እና መላው ህዝብ ብርቱ ተጋድሎ በእጅጉ የጠየቀ ነውም ብለዋል፡፡
የጀግና ሽልማቱ በነጻነት ኮርታ የምትቀጥል ለትውልድ የምትሻገር አገር ፣ የሰላም አየር የሚተነፍስ ትውልድ መቀጠሉን ማየት ነውም ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!