Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ፖሊስ የጤና ጉዳተኞች ማገገሚያ ማዕከል ለማስገንባት የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

የፌዴራል ፖሊስ የጤና ጉዳተኞች ማገገሚያ ማዕከል ለማስገንባት የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሠራዊቱ የጤና ጉዳተኞች ማገገሚያ እና ማስተናበሪያ ማዕከል ለማስገንባት ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት÷ ፌዴራል ፖሊስ በመንግስትና በህዝብ የተሰጠውን ሀገራዊ ግዳጅ በመቀበል በሁሉም አቅጣጫ አስፈላጊውን መስዋዕትነት እየከፈለ ኢትዮጵያን እየጠበቀ ያለ ተቋም ነው፡፡ በዚህ ሀገራዊ ተልዕኮ ውስጥ በርካታ አመራሮቻች እና አባላት የሚያጋጥማቸው ጉዳቶችና አደጋዎች ቀላል እንዳልሆኑ አንስተዋል፡፡ የአካል ጉዳት አጋጥሟቸው በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል ህክምና ወስደው ከጨረሱ በኋላ ለሚቀጥለው ፖሊሳዊ ተልዕኮ እንዲዘጋጁ የሚያደርግ ማገገሚያና የማስተናበሪያ ማዕከል በተቋሙ አለመኖሩንም ጠቁመዋል፡፡ ባለፉት 27 ዓመታት ግን ወያኔ ተቋም እንዲገነባ ስለማይፈለግ ለሀገርና ለሠራዊቱ ይጠቅሙ የነበሩ ተቋማትን አፍርሶ ሠራዊታችን በተለያዩ ግዳጆች ላይ የአካል ጉዳት በሚያጋጥምበት ወቅት ከህክምና አገልግሎት በኋላ የሚያገግምበት ማዕከል ባለመኖሩ ለችግር ሲዳረግ ነበር ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሠራዊቱ ለሀገራችን በሚከፍለው መስዋዕትነት ልክ ሀገሩ ውለታ መዋል ስለሚኖርባት ማዕከሉን ለማስገንባት ኃላፊነት ወስደን እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌና ሌሎች የኮርፖሬሽኑ ማነጅሜንት የሀገራችን ሉዓላዊነት ለማስከበር ሲሉ አጥንታቸውን ለከሰከሱ፣ ደማቸውን ላፈሰሱ የሠራዊቱ አባላት ማዕከሉን ለማስገንባት ትብብር በማድረጋቸውም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የማዕከሉ ግንባታ በዚህ ዓመት አልቆ ለስራ እንደሚበቃ የገለፁት ኮሚሽነር ጀነራሉ÷ አገልግሎቱንም ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ብቻ ሳይሆን ለክልል ፖሊስ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ዮናስ አያለው በበኩላቸው÷ የሠራዊቱ አመራርና አባላት ውድ ህይወታቸውን መስዋዕት በማድረግና በገንዘብ የማይገመት አገልግሎት በመስጠት ሀገርን ከጠላት እየጠበቁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ማነጅመንት አባላት የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር ሲሉ ጉዳት የደረሰባቸውን የሠራዊቱን አባላት ማገዝ እንዳለብን በመስማማት የማዕከሉን ዲዛይን በአጭር ጊዜ ውስጥ አዘጋጅተን በማቅረብ የመግባቢያ ስምምነቱ መፈረሙን ተናግረዋል፡፡ ማዕከሉ ኮልፌ ቀራኒዮ በሚገኘው የቀድሞ ፈጥኖ ደራሽ ማሰልጠኛ ግቢ በ64 ካሬ ሜትር ላይ እንደሚገነባ መገለጹን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሠራዊቱ የጤና ጉዳተኞች ማገገሚያ እና ማስተናበሪያ ማዕከል ለማስገንባት ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
 
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት÷ ፌዴራል ፖሊስ በመንግስትና በህዝብ የተሰጠውን ሀገራዊ ግዳጅ በመቀበል በሁሉም አቅጣጫ አስፈላጊውን መስዋዕትነት እየከፈለ ኢትዮጵያን እየጠበቀ ያለ ተቋም ነው፡፡
 
በዚህ ሀገራዊ ተልዕኮ ውስጥ በርካታ አመራሮቻች እና አባላት የሚያጋጥማቸው ጉዳቶችና አደጋዎች ቀላል እንዳልሆኑ አንስተዋል፡፡
 
የአካል ጉዳት አጋጥሟቸው በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል ህክምና ወስደው ከጨረሱ በኋላ ለሚቀጥለው ፖሊሳዊ ተልዕኮ እንዲዘጋጁ የሚያደርግ ማገገሚያና የማስተናበሪያ ማዕከል በተቋሙ አለመኖሩንም ጠቁመዋል፡፡
 
ባለፉት 27 ዓመታት ግን ወያኔ ተቋም እንዲገነባ ስለማይፈለግ ለሀገርና ለሠራዊቱ ይጠቅሙ የነበሩ ተቋማትን አፍርሶ ሠራዊታችን በተለያዩ ግዳጆች ላይ የአካል ጉዳት በሚያጋጥምበት ወቅት ከህክምና አገልግሎት በኋላ የሚያገግምበት ማዕከል ባለመኖሩ ለችግር ሲዳረግ ነበር ብለዋል፡፡
 
በአሁኑ ወቅት ሠራዊቱ ለሀገራችን በሚከፍለው መስዋዕትነት ልክ ሀገሩ ውለታ መዋል ስለሚኖርባት ማዕከሉን ለማስገንባት ኃላፊነት ወስደን እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌና ሌሎች የኮርፖሬሽኑ ማነጅሜንት የሀገራችን ሉዓላዊነት ለማስከበር ሲሉ አጥንታቸውን ለከሰከሱ፣ ደማቸውን ላፈሰሱ የሠራዊቱ አባላት ማዕከሉን ለማስገንባት ትብብር በማድረጋቸውም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
የማዕከሉ ግንባታ በዚህ ዓመት አልቆ ለስራ እንደሚበቃ የገለፁት ኮሚሽነር ጀነራሉ÷ አገልግሎቱንም ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ብቻ ሳይሆን ለክልል ፖሊስ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ዮናስ አያለው በበኩላቸው÷ የሠራዊቱ አመራርና አባላት ውድ ህይወታቸውን መስዋዕት በማድረግና በገንዘብ የማይገመት አገልግሎት በመስጠት ሀገርን ከጠላት እየጠበቁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
 
የኮርፖሬሽኑ ማነጅመንት አባላት የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር ሲሉ ጉዳት የደረሰባቸውን የሠራዊቱን አባላት ማገዝ እንዳለብን በመስማማት የማዕከሉን ዲዛይን በአጭር ጊዜ ውስጥ አዘጋጅተን በማቅረብ የመግባቢያ ስምምነቱ መፈረሙን ተናግረዋል፡፡
 
ማዕከሉ ኮልፌ ቀራኒዮ በሚገኘው የቀድሞ ፈጥኖ ደራሽ ማሰልጠኛ ግቢ በ64 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ እንደሚገነባ መገለጹን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.