አሸባሪው ህወሓት እየፈጸመ ያለውን ግፍ ለማስቀረት የትግራይ ተወላጆች ከምን ጊዜውም በላይ መንቀሳቀስ ይገባቸዋል-ዶ/ር አረጋዊ በርሄ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሃት ቡድን በትግራይ እና በመላው ኢትዮጵያ እየፈጸመ ያለውን ግፍ ለመከላከል እና ለማስቀረት በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ ያሉ የትግራይ ተወላጆች ከምን ጊዜውም በላይ እጅ ለእጅ ተያይዘው መንቀሳቀስ ይገባቸዋል ተባለ።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪ ዶክተር አረጋዊ በርሄ ÷ የትግራይ ህዝብ ልጆቹን ዳግም በጦርነት ለሚማግድበት የሽብር ቡድን ህወሃት ጆሮውን ሳይሰጥ ቡድኑን በመገርሰስ ነጻነቱን ለማወጅ በአንድነት ሊንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።
ይህንን ለማድረግም ከሌሎች ወንድምና እህት ኢትዮጵያውያን ጋር መተባበር ይገባቸዋል ነው ያሉት።
ሽብርተኛው ህወሃት ለዘመናት ለራሱ የስልጣን ጥም እና ፍላጎቱን ለማሳካት ብቻ ባለመ መልኩ የትግራይን ህዝብ በአምባገነናዊ አስተዳደር ስር እንዲማቅቁ ማድረጉንም አንስተዋል ዶክተር አረጋዊ በርሄ፡፡
በዚህም በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በቡድኑ ሰቆቃ እና ችግር ውስጥ ያለውን ህዝባቸውን ከዚህ ለማውጣት ባሉበት ሁሉ ድምጽ እንዲሆኗቸው ነው የጠየቁት።
በአፈወርቅ አለሙ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!