Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው በቴክኖሎጂ ዘርፍ የዓለም አቀፉን የገበያ ፍላጎት ታሳቢ ባደረገ ስራ ላይ እንዲሰማራ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014፣ (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራውን በቴክኖሎጂ ዘርፍ የቢዝነስ አማራጮች እንዲሰማራና በሀገር ውስጥ ካሉ ባለሙያዎች ጋር እንዲተዋወቅ የሚያደርግ የበይነ መረብ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፥ ዳያስፖራው የውጪ ምንዛሬ በሚያስገኝ፣ ለወጣቶች የስራ እድል በሚፈጥርና የዓለም አቀፉን የገበያ ፍላጎት ታሳቢ ባደረገ ስራ ላይ እንዲሰማራ ጠይቀዋል፡፡

መንግስት በግሉ ዘርፍ የሚመራ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት በትኩረት እየሰራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ የግሉ ዘርፍ እና ዳያስፖራው በዘርፉ ለሚያደረጉት እንቅስቃሴ ሁሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የዲጂታል የስራ እድል ፈጠራ እየሰፋ በመምጣቱ ወጣቶችን ለዚህ ስራ ዝግጁ ማድረግ እንደሚገባ እና በቅንጅት መስራት ወሳኝ መሆኑ መገለፁንም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.