Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ የፖለቲካ፣ ጸጥታና በድርቅ ምላሽ ዙሪያ ላይ ተውያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ የፖለቲካ፣ ጸጥታና በድርቅ ምላሽ ዙሪያ ላይ ተወያይተዋል፡፡

አመራሩ በሀገሪቱ እና በክልሉ ፖለቲካዊ ሁኔታ ላይ በተለይም በአገራዊ ምክክሩ ዝግጅት ላይ በሰፊው መወያየታቸው ተገልጿል።

በውይይቱ እንደ ክልል ከቀድሞ ሥርዓቶች የተወረሱ ላላቸው የፖለቲካ ችግሮች መፍትሄ የሚያንጸባርቅና የህዝቡን የረጅም ጊዜ ጥያቄዎች የሚመልሱ ጉዳዮች በብሔራዊ ምክክሩ አጀንዳዎች አካል እንዲሆን ከመግባባት ላይ ተደርሷል።

በተጨማሪም የሶማሌ ክልል ህዝብ ሃሳቦችን አንድ የሚያድረግ ክልላዊ ውይይት እንዲጀመርም ከስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን፥ በሌላ በኩል የክልሉ ሰላምና የሀገሪቱ ድንበር ጸጥታ ለማጠናከርም ምንም አይነት ድርድር የማያስፈልግ ጉዳይ መሆኑንም በውይይቱ ላይ ተገልጿል ።

በክልሉ የተከሰተውን የድርቅ ሁኔታ በተመለከተም እስካሁን የተሰጠው የድርቁ ምላሽ በተለይ የዞን እና የወረዳ አስተዳደሮች ያከናወኗቸው ሥራዎች አበረታች በመሆናቸው በድርቁ የሰዎችና የእንስሳት ህይወት እንዳይጠፋ ምላሹ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተወስኗል።

እንዲሁም፥ የእንስሳትን ህይወት ከድርቁ ለመታደግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ ዳያስፖራ፣ ነጋዴውና የሀገሪቱ ማህበረሰብም የበኩላቸውን ተሳተፎ እንዲያደርጉ አመራሩ ጥሪ ማቅረቡን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.