Fana: At a Speed of Life!

የጌዴኦ ዞን በድርቅ ለተጎዱ የቦረና ዞን ነዋሪዎች ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጌዴኦ ዞን ከነዋሪዎች ያሰባሰበውን 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ በድርቅ ለተጎዱ የቦረና ዞን ነዋሪዎች አበርክቷል።
 
ድጋፉ 100 ኩንታል በሶ፣ 50 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት፣ 1 ሺህ ደርዘን እሽግ ውሃን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
በተጨማሪም የጌዲኦ ዞን ነዋሪዎች በድርቅ ለተጎዱ 200 ኩንታል የተቀነባበረ የእንስሳት መኖ እንዲሁም 200 ቶን ሳር ነው ያበረከቱት።
 
በቀጣይ ሌሎች ድጋፎች የሚቀጥሉ መሆኑን በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጌዴኦ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ዝናቡ ወልዴ ተናግረዋል።
 
በዞኑ ገደብ ወረዳ ያሉ የቦረና ከብቶችም አስፈላጊው የህክምናና ሌሎች እንክብካቤዎች እንደሚደረግላቸው ነው የገለጹት።
 
የቦረና ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበዱሰላም ዋሪዮ በበኩላቸው÷ ለተደረገው ድጋፍ በቦረና ህዝብ ስም አመስግነዋል።
 
የጌዴኦ አባ ገዳዎች ነገ ለሚከበረው የጌዴኦ ዘመን መለወጫ በዓል አስቀድሞ አምላክ የሚወደዉን ድጋፍ ለማበርከት እንደሆነ በርክክቡ ጊዜ ተናግረዋል።
 
በቢቂላ ቱፋና ጌታቸዉ ሙለታ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.