ለጥምቀት በዓል ከ5 በላይ ታቦታት ማደሪያ የሆነውን የአበበ ቢቂላ ስታዲየም የማጽዳት ስራ ተከናወነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የጥምቀት በዓልም ምክንያት በማድረግ ከ5 በላይ ታቦታት ማደሪያ የሆነውን የአበበ ቢቂላ ስታዲየም የማፅዳት ስራ ተከናወነ፡፡
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ሽታዬ መሐመድ÷በክፍለ ከተማው የአካባቢን ፅዳት ለመጠበቅ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡
በክፍለ ከተማው የወረዳ 5 ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ሽፈራው በበኩላቸው ÷ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ታቦታት ለጥምቀተ ባህሩ የሚያርፉበት በመሆኑ የወረዳውን ነዋሪዎችና የክፍለ ከተማን አመራሮች ያሳተፈ የፅዳት ዘመቻ መካሄዱን ገልጸዋል፡፡
የዛሬው የፅዳት ዘመቻ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን የገለጹት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ÷ መደበኛው የጽዳት ስራም ቀኑን ጠብቆ እየተካሄደ ነው ማለታቸውን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!