የመረጃ አያያዝ ስርዓትን በማዘመን ህገ ወጥነትን መከላከል ይገባል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለከተማ ቤቶች አስተዳደር ስርዓት የሚያገለግል ሶፍት ዌር በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለምቶ በይፋ የስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡
የለውጡ አመራር ወደ ስራ ሲገባ ተግባራዊ ሊያደርጋቸዉ ቃል ከገባባቸዉ ጉዳዮች መካከል አንዱ አሰራሮችን ቀልጣፋና ግልፅ ማድረግ በመሆኑ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ለማዘመን ዛሬ ተግባራዊ የሆነው ሶፍትዌር አንዱ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡
ህብረተሰቡ የሚፈልገውን አገልግሎት በአግባቡ ለመስጠት ሶፍት ዌሩ ላይ የሚገቡ መረጃዎችን ከመሰብሰብ ጀምሮ አጠቃላይ ተግባራዊነቱ ላይ ትኩረት በመስጠት ሊሰራ ይገባልም ብለዋል፡፡
ፍትሃዊነትን ለማስፈንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ለትክክለኛ መረጃ አያያዝ የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮችን መጠቀም ጥቅሙ የጎላ እንደሆነ ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የከተማ አስተዳደሩ በከተማው የሚገኙ ቤቶችን በዚህ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ሶፍትዌር አማካኝነት ሌብነትና ህገ ወጥነት እንዳይስፋፋ ይሰራልም ነው ያሉት፡፡
ሶፍት ዌሩ የቀበሌ ቤቶች፣ ኮንደምንየሞች፣ ማህበራት ቤቶችና ክፍት ቦታዎች ያሉበትን ቦታ በመመዝገብ በመረጃ ስለሚይዝ የፋይል መጥፋትና መሰል ችግሮችን ይቀርፋል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!