Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ዞን ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ስራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን ባለፉት ስድስት ወራት ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል አስመዝግበው የኢንቨስትመንት ፈቃድ የወሰዱ ወደ ስራ መግባታቸውን የዞኑ አስተዳዳር ገለጸ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ ለኢዜአ እንደተናገሩት ፥ በዞኑ ኢንቨስትመንትን ለማሳደ የተለያዩ ማበረታቻዎች በመደረግ ላይ ይገኛል።

በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት 13 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ልማት መግባታቸው ተገልጿል።

ባለሀብቶቹ በሂደት የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመቅረፍ በኢንቨስትመንት አፈፃፀም ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከር መፍትሄ የመስጠት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ቦታ ተረክበው በወቅቱ ወደልማት በማይገቡ ባለሀብቶች ላይ ደግሞ የኢንቨስትመንት አዋጅና ደንብ በሚፈቅደው መሠረት እርምጃ እየተወሰደ ነውም ብለዋል።

የዞኑ ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደመቀ ኩኬ በበኩላቸው ፥ ባለሀብቶቹ ከተሰማሩባቸው የስራ መስኮች መካከል አገልግሎት፣ የግብርና ልማት፣ ጤና እና ኢንዱስትሪ ዘርፎች ተጠቃሽ ናቸው።

ፈቃድ የወሰዱት በለሀብቶች 100 ሄክታር በገጠር እንዲሁም 11 ሺህ ካሬ ሜትር የከተማ ቦታ ተረክበው ወደ ማልማት መግባታቸውን ነው አቶ ደመቀ የተናገሩት።

በአሁኑ ወቅት ባለሃብቶቹ እያደረጉት ባለው የልማት እንቅስቃሴ ከ4 ሺህ 500 ለሚበልጡ ዜጎች ጊዜያዊና ቋሚ የስራ እድል ፈጥረዋል ነው የተባለው።

ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው በሙሉ አቅማቸው ወደ ማምረትና አገልግሎት ሲሸጋገሩ ለ7 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩም ተገልጿል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.