የበርበራ -ኢትዮጵያ ንግድ ኮሪደር ለሀገራችን ገቢና ወጪ ንግድ ተወዳዳሪ አገልግሎት በሚሰጥበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የበርበራ -ኢትዮጵያ ንግድ ኮሪደር ለሀገራችን ገቢና ወጪ ንግድ ተወዳዳሪ አገልግሎት በሚሰጥበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ ከሶማሊላንድ የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ፥ የበርበራ – ኢትዮጵያ የንግድ ኮሪደር ለሀገራችን ገቢና ወጪ ንግድ ተወዳዳሪ አገልግሎት የሚሰጥበትን ሁኔታ እና በበርበራ ወደብ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ መክረዋል።
ውይይቱ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከበርበራ ወደብ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ የስራ ግንኙነት በማጠናከር በቀጣይ በትብብር አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከዚህ ባለፈም ድርጅቱ እየሰጠ ስለሚገኘው አገልግሎት፣ የደረቅ ወደቦች ግንባታ እና የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች በተመለከተ አቶ ሮባ ለልዑካን ቡድኑ ገለጻ ማድረጋቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!