የሀገራችንን ቅርሶች ለመጠበቅና የቅርስ ባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት የሚረዳ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ፖርቹጋል እና ሞናኮ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሄኖክ ተፈራ ከዓለም አቀፉ የሐውልቶችና ታሪካዊ ቦታዎች ምክር ቤት (ICOMOS) ፕሬዚዳንት ቴሬሳ ፓትሪሲዮ ጋር ውጤታማ ውይይት ማካሄዳቸውን ገለጹ፡፡
አምባሳደሩ ÷ ኢትዮጵያ ከምክር ቤቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር መስማማታቸውንም ነው የጠቆሙት፡፡
በቀጣይም የሀገራችንን ቅርሶች ለመጠበቅና የዓለምአቀፍ እውቅና እንዲያገኙ ለማድረግ የሀገራቸንን የቅርስ ባለሙያዎች አቅም በመገንባት ለማብቃት እንደሚሰሩ ነው ያመላከቱት፡፡
ዓለም አቀፉ የመታሰቢያ ሐውልቶች እና ታሪካዊ ቦታዎች ምክር ቤት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሣይንስ እና የባህል ድርጅትን በዓለምአቀፍ የቅርፅ ጥበቃ ላይ እንደሚያማክር ከፈረንሳይ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዓለም አቀፍ የሐውልቶች እና ታሪካዊ ቦታዎች ምክር ቤት (ICOMOS) በዓለም ላይ ያሉ ታወቂ ሐውልቶችን እና ታሪካዊ ቦታዎችን የመጠበቅና የመንከባከብ ዓላማ ያለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።