ወጣቶች እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ለበጎነትና መልካምነት በማዋል በሃገር ግንባታ ውስጥ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል – አቶ ታዬ ደንደአ
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ የበጎ ፍቃድ ወጣቶች ምረቃ መርሃ ግብር በጅማ ዩኒቨርስቲ ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደ እና የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ጀማል አባ ፊጣን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
በስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ታዬ፥ ወጣቶች የራሳቸው ብቻ ሳይሆኑ የማህበረሰቡም ጭምር እንደሆኑ ሊያውቁ ይገባል ብለዋል።
በመሆኑም እውቀታቸውና ጉልበታቸውን ለመልካም ተግባር በማዋል በሃገርና በማህበረሰብ ግንባታ ውስጥ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባ ፊጣ በበኩላቸው፥ ወጣቱ ትውልድ ምክንያታዊነትን በማጠናከር፣ የስራ ባህል ክህሎትን በመላበስ ለሃገራዊ አንድነትና ብሄራዊ መግባባት በግንባር ቀደምትነት ሊሰለፍ ይገባል ብለዋል።
በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት 1 ሺህ 700 ወጣቶች ለ45 ቀናት በሰላም፣ በአብሮነትና በጎነት ዙርያ ስልጠና ሲወስዱ እንደነበር ተገልጿል።
ለቀጣይ ዘጠኝ ወራትም ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመሆን በተለያዩ ክልሎች ተዘዋውረው ህብረተሰቡን እንደሚያገለግሉ ተገልጿል።
በሙክታር ጠሃ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!