Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የመላ ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተምሳሌት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡

የናሬንድራ ሞዲ የኢትዮጵያ ጉብኝት የኢትዮዽያና ሕንድን የቆየ ታሪካዊ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የሚያሸጋግር ነው፡፡

ኢትዮጵያ እና ሕንድ በዲፕሎማሲ፣ ኢኮኖሚ፣ ባሕልና ሌሎች ዘርፎች ያላቸው ግንኙነት የረጅም ጊዜ ታሪክ ያስቆጠረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከትናንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.