አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ከዓለምአቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር ልዑክ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር የኢትዮጵያ ሀላፊ ከሆኑት ኒኮላስ ቮን አርክስ ጋር ተገናኝተው ተወያዩ፡፡
ርዕሰ-መስተዳድሩ ከሃላፊው ጋር በክልሉ ላጋጠመው የድርቅ አደጋ ምላሽ መስጠት በሚቻልበት ሂደት ላይ መምከራቸውን ነው የጠቆሙት፡፡
አያይዘውም “ማኅበሩ ለእንስሳት ክትባትና መኖ ለማቅረብ ፕሮጀክት ነድፎ በላጋሂዳ፣ ቁቢ እና ማያ ሙሉቆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በመስማቴ ከፍተኛ ደስታ ተስምቶኛል” ማለታቸውን በትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩት መልዕክት ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!