Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ነገ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ተገኝተው የመንግሥትን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡

በተጨማሪም ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.