Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የታየው መተባበር በሌሎችም ዘርፎች ሊደገም ይገባል – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ያሳዩትን መተባበርና አንድነት በልማት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ሊደግሙት ይገባል ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ገለጹ።

ማኅበረሰቡ የአካባቢውን ሠላም እና ደህንነት ለማስጠበቅም ያሳየው ተሞክሮ ልምድ ሊወሰደበት እንደሚገባ ነው ምሁራኑ የተናገሩት፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሕግ እና አስተዳዳር ኮሌጅ መምህር ደረጀ ፍቅሬ÷ ከልምድ መቅሰም ባሻገር በሁሉም አካባቢዎች ሠላምና ደንኅነትን ለማስጠበቅ ጠንካራና የተቀናጀ ስራ መስራት ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን የሚያስተምር ነው ብለዋል፡፡

በጉባኤው የተገኙ ልምዶችን በኢኮኖሚው እና በዲፕሎማሲው ዘርፍ መድገም ከሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ይጠበቃል ያሉት ደግሞ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ሴነሳ ደምሴ ናቸው።

አዲስ አበባ ከተማ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ማረጋገጥ የተቻለውን ሠላም እና መረጋጋት በሁሉም አካባቢዎች ተግባራዊ በማድረግም መድገም ይገባል ብለዋል።

በሠላምና ደኅንንት ዙሪያ የኢትዮጵያውያን አንድ መሆን ለማኅበራዊ፣ ለፖለቲካ እና ለኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ነው ብለዋል ምሁራኑ፡፡

በአልማዝ መኮንን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.