Fana: At a Speed of Life!

በምርጫው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሸናፊነቱን አረጋግጧል – ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባሳየው ቁርጠኝነት አሸናፊነቱን አረጋግጧል አለ።
የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የምርጫ ጉዳዮች ኃላፊ ምርጫው ስንሻው እንዳሉት ፥በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ ትልቅነቱን፣ሰላም ወዳድነቱንና አሸናፊነቱን አረጋግጧል።
ሕዝቡ ኢትዮጵያ እድሎቿም ፈተናዎቿም ፊት ለፊቷ ናቸው በሚል የተደገሰውን ጥፋት በማሸነፍ በሰላማዊ ምርጫ ተሳትፎ መንግሥት ለማቋቋም ቁርጠኛ እንደሆነ ማሳየቱን አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሰላም እና አንድነት ያለውን ጥረት አላጓደለም፤ ለዚህም ምስጋና ይገባዋል ነው ያሉት።
ሰላማዊ ሽግግር እንዲኖር ትብብሩ ጥረት ማድረጉን ጠቅሰው÷ በምርጫው በሰላም የምንታገል ሃይሎች መሆናችንን ለዓለም ማሳየት ችለናል ብለዋል፡፡
ሕዝቡ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የነበሩበትን ከፍተኛ ጫናዎች በመቋቋም የኢትዮጵያ ጠላቶችን ቅስም የሰበረ ምርጫ ማከናወኑን አስገንዝበዋል፡፡
ሕዝቡ ፍላጎቱ ሰላም በመሆኑ ምርጫው በስኬት ተጠናቅቋል፤ በዚህም የአፍሪካ ህብረት፣የአውሮፓ ህብረት፣ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጃፓንና በርካቶች ለልፋታችን እውቅና ሰጥተዋል ነው ያሉት፡፡
አዲሱ መንግሥት እስከሚመሰረትበት መጪው መስከረም ወር ድረስ ያለው የሽግግር ጊዜ ሰላማዊ እንዲሆን፣ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማረጋገጥና ጸጥታ የማስከበር ኃላፊነቱን በቁርጠኝነት እንዲወጣ ጠይቀዋል።
በሶስና አለማየሁ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.