Fana: At a Speed of Life!

በቴፒ የሽፍታ ቡድን በመምራት የአካባቢውን ሰላም ሲያውክ የነበረው ግለሰብና ግብረ አበሮቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በግድያና በሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ ሁለት የፖሊስ አባላትን ጨምሮ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
 
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ገፅታ ግንባታ ዲቪዥን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ እንደገለፁት÷ የክልሉን ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ወንጀለኞችን የማደን ተልእኮ ተካሂዷል ።
 
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማና አካባቢው ባለፋት ሶስት አመታት የወንጀል ተግባር በማስተባበር፣ ንፁሃንን በመግደል፣ ንብረት በማውደም እንዲሁም ነዋሪዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት በመሆን የተጠረጠሩና በሽፍትነት የተሰማሩ አምስት ግለሰቦች መያዛቸውን ተናግረዋል ።
 
ተጠርጣሪዎቹ የግል ጥቅምን ለማግኘት በማሰብ በቴፒና አካባቢው ሰላም እንዳይኖር ሲያደርጉ እንደነበር አስታውሰዋል።
 
“የሽፍታ ቡድኑን ሲመራና ትዕዛዝ ሲሰጥ የነበረ የአካባቢውን ሰላም በማወክ ከፍተኛ ሚና የነበረው ግለሰብ ከሁለት ግብረ አበሮቹ ጋር በቴፒ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ተናግረዋል ።
 
ከህዝብና መንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ወደጎን በመተው ከቡድኑ ጋር በጥቅም በመተሳሰር በህገወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሁለት የፖሊስ አባላትም በቁጥጥር ስር እንደዋሉ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
በቁጥጥር ስር በዋሉት ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት ምክትል ኢንስፔክተሩ÷ወንጀለኞችን ተከታትሎ ወደ ህግ የማቅረብ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.