Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ ሚ ዐቢይ ለምክር ቤቱ የሰጡት ምላሽ ግልጽነትን ፈጥሮልናል ሲሉ የባህር ዳር ነዋሪዎች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ በሕዝቡ ዘንድ የነበሩ ብዥታዎችን ግልጽ እንዲሆኑ አድርጓል ሲሉ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት÷ የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ነባር አመራሮች የነበሩ ግለሰቦች መፈታት የተደበላለቀ ስሜት እና ቅሬታ ፈጥሮ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ግለሰቦቹ የተፈቱበትን ሁኔታ ለምክር ቤቱ ሲያብራሩ÷ የተገኘውን ድል ለማፅናትና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት መሆኑን በገለጹበት ወቅት በግለሰቦቹ አፈታት ላይ ነዋሪዎቹ የነበራቸውን ስሜት እንደቀየረው ነው የገለጹት፡፡
በተለይም ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ድርድር እየተደረገ ነው በሚል የሚናፈሰውን ወሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ግልፅ ማድረጋቸው ተገቢና ወቅታዊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሁኔታዎችን በስሜት ሳይሆን በስሌት ማየትና መወያየት መፍትሄ እንዳለው ቢታመንም÷ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ለመደራደር አሁን ላይ ያለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ይፈቅዳል ብለው እንደማያምኑም ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ አገራዊ ምክክርን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት ምላሽ ትክክለኛና የሚያስማማ መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ማክሰኞ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ መስጠታቸው ይታወቃል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.