በቤንች ሸኮ ዞን አንዲት እናት በአንዴ 4 ህጻናትን ተገላገሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንች ሸኮ ዞን አንዲት እናት አራት ህጻናትን በአንዴ በሰላም ተገላገሉ፡፡
በዞኑ በሰሜን ቤንች ወረዳ በኮሶኮል ቀበሌ ልዩ ስሙ ሽችን መንደር ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ አብነሽ ካይትናብ÷ 3 ወንድና 1 ሴት ልጅ በድምሩ አራት ህጻናትን በሰላም መገላገላቸውን በወረዳው የያሊ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ሽፈራው ዳካ ተናግረዋል።
በአሁኑ ሰአት አራቱም ህጻናት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የጠቆሙት ኃላፊው፥ ህጻናቱም ከ1 ነጥብ 39 ኪሎ ግራም እስከ 1 ነጥብ 815 ኪሎ ግራም ክብደት እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!