ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ከጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪና ሴሬኒን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል::
በውይይታቸውም÷ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡