ቻይና በ2022 ከፍተኛ የግብር ማሻሻያ ልታደርግ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በ2022 የ 173 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የግብር ቅናሽ ልታደርግ መሆኗን አስታወቀች፡፡
የቻይና ገንዘብ ሚኒስትር ሊዩ ኩን ÷ ቻይና ቅናሹን የምታደርገው በቴክኖሎጂ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በሰብዓዊ ዘርፍ፣ በዘመናዊ ግብርና እና በቀጠናዊ ጉዳዮች እና መሰል ዘርፎች ላይ የሚሰሩትን ለመደገፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከግብር ቅናሹ በዋናነት ተጠቃሚ ይሆናሉም ነው የተባለው፡፡
የቻይና መንግስት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመደጎም 3 ቢሊየን ዩዋን (የቻይና መገበያያ ገንዘብ) ከወዲሁ መመደቡንም ምክትል ገንዘብ ሚኒስትሩ ዩ ዌይፒንግ መግለጻቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡